በተለያዩ ወንጀሎች በመንግስትና በሕዝብ ሀብት ላይ የደረሰ ጉዳት ለማዳን በአጠቃላይ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ መዝገቦች ላይ ምርመራ መደረጉ ተገለፀ

You are currently viewing በተለያዩ ወንጀሎች በመንግስትና በሕዝብ ሀብት ላይ የደረሰ ጉዳት ለማዳን በአጠቃላይ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ መዝገቦች ላይ ምርመራ መደረጉ ተገለፀ

AMN – ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም

በሽብርተኝነት፣ በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችና በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች በመንግስትና በሕዝብ ሀብት ላይ የደረሰ ጉዳት ለማዳን በአጠቃላይ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ መዝገቦች ላይ ምርመራ መደረጉን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ተወካይ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ ገልፀዋል፡፡

መምሪያው ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ፤ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡

በዚህም ወቅት አቶ ሙሊሳ አብዲሳ አያይዘው በሩብ ዓመቱ ከቀረቡ 802 አዳዲስ ጥቆማዎች ውስጥ 660 የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን ጠቁመው፤ በወንጀል ድርጊት ከተጠረጠሩ 3594 ተፈላጊዎች መካከል ደግሞ 1784 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን መናገራቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ 81,461 የፎረንሲክ ምርመራ ጥያቄዎች ቀርበው 81,289 ምርመራቸው የተከናወኑ መሆናቸውን አንስተው ጠቅላይ መምሪያው ከሁሉም የክልል ክላስተሮችና ከሌሎች የፍትህ እና የፀጥታ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት አመርቂ ውጤት በማስመዝገቡ ከሁሉም የክልል ክላስተሮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት ማግኘቱም ተገልጿል።

አቶ ሙሊሳ አብዲሳ የተሰጠንን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ታማኝና ግልፅ ለማድረግ በታክቲክና በፎረንሲክ ምርመራ የተገኙ ዉጤቶችን አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ማለታቸውም ተጠቅሷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review