በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት በርንሌይን የገጠመው አርሰናል 2ለ0 አሸንፏል።
ቪክቶር ዮኬሬሽ እና ዴክለን ራይስ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
በዚህም ጨዋታ ግብ ያልተቆጠረበት አርሰናል ከ10 ጨዋታ 25 ነጥብ በመሰብሰብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከሦስት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥሏል።
በሲቲ ግራውንድ ኖቲንግሃም ፎረስትን የገጠመው ዩናይትድ 2ለ2 ተለያይቷል።
የዩናይትድን ግቦች ካሲሜሮ እና አማድ ዲያሎ ከመረብ አሳርፈዋል።
የፎረስትን ሁለት ግቦች ሞርጋን ጊብስ ዋይት እና ሳቮና አስቆጥረዋል።
ክሪስታል ፓላስ ብሬንት ፎርድን 2ለ0 ሲያሸንፍ ፣ ብራይተን ሊድስን 3ለ0 ረቷል።
ፉልሃም ወልቭስን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል።
በሸዋንግዛው ግርማ