ሰላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢን እዉን በማድረግ ምክንያታዊ ትዉልድ ለመፍጠር በቅንጅት መስራት ይገባል

You are currently viewing ሰላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢን እዉን በማድረግ ምክንያታዊ ትዉልድ ለመፍጠር በቅንጅት መስራት ይገባል

AMN – ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢን እዉን በማድረግ የሀገርን የትምህርት ስብራት የሚጠግን ምክንያታዊ ትዉልድን ለመፍጠር በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ዙሪያ ከግል ትምህርት ቤቶች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እየመከረ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ፣ በመዲናዋ ትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እዉን በመደረጉ የተሻሉ ዉጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ከአዋኪ ድርጊቶች በመራቅ በአመለካከት የዳበረ እና በስነ ምግባርም የታነፀ ዜጋን በማነፅ በኩል በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም፤ ትምህርት ቤቶች ከማንኛውም አመለካከት ገለልተኛ ሆነዉ ምክንያታዊ እና በሀገር ግንባታ ላይ አሻራን የሚያስቀምጥ ትዉልድ ግንባታ ላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለሰላማዊ የመማር ማስተማር የሚያደርገዉን አበርክቶ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ተወካይ እና የቢሮዉ ምክትል ሀላፊ አቶ አሊ ከማል በበኩላቸው፤ መድረኩ በጋራ በመመካከር ለቀጣይ የትምህርት ተቋማቱ የመማር ማስተማር ሰላማዊነት መግባባት የሚደረስበት ነዉ ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review