በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ

You are currently viewing በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ

AMN-ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በ4ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም 7 ሰዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ከባለፈው ዓመት የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ጋር ይጫወታል።

በባህርዳር ከተማ ተሸንፎ የጀመረው ሀዲያ ሆሳዕና ቀጥሎ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።

በግብፁ ክለብ ፒራሚድስ ተሸንፎ ከካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ውጪ የሆነው ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ያደረገው አንድ ጨዋታ ብቻ ነው።

በመክፈቻ ጨዋታ አዳማን ገጥሞ 0ለ0 መለያየቱ ይታወሳል።

10 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሸገር ከተማን ይገጥማል።

ከኢትዮጵያ መድን ጋር ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ጊዮርጊስ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፏል።

ከከፍተኛ ሊግ ያደገው ሸገር ከተማ ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ተሸንፎ በሌላኛው አቻ ተለያይቷል።

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት መቀለ 70 እንደርታ ከሃዋሳ ከተማ ይጫወታል።

ሁለቱ ክለቦች ተመሳሳይ ሦስት ጨዋታዎችን አከናውነው ሃዋሳ ስድስት ነጥብ ሲሰበስብ ፣ መቀለ አንድ ነጠብ ብቻ ይዟል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review