በጎነት ለሀገር ሰላምና እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው

AMN – ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በጎነት ግንኙነትን በማጠናከር ለሀገር ሰላምና እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ ከ500 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የበጋ የበጎ ፈቃድ መርሃግብር በይፋ ተጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ 42.5 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዋል።

በጎነት ግንኙነትን በማጠናከር ለሀገር ሰላምና እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሯ፤ በከተማችን ወጣቱንና መላ ነዋሪውን እያሳተፍን በተገበርነው የበጎነት አገልግሎት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግዳሮቶችን እየተሻገርን የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት ቀይረናል ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!” በሚል መሪ ሀሳብ 500 ሺህ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት ነዉ ብለዋል፡፡

ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበጋውን የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በመድረኩ ላይ የሚመለከታችዉ አካላት እና በጎ ፍቃደኞች ተገኝተዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review