ፓሪሰን ዠርማ ከባየርን ሙኒክ፦ ሌላው የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ

You are currently viewing ፓሪሰን ዠርማ ከባየርን ሙኒክ፦ ሌላው የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ

AMN-ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

የባለፈው ዓመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባለ ድል ፓሪሰን ዠርማ ባየርን ሙኒክን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ክለቦች የዘንድሮ አጀማመራቸው ገና ከወዲሁ ብዙ እርቀት እንደሚጓዙ ማሳያ ሊሆን ይችላል።

የመጀመሪያ ሦስት መርሃግብራቸውን በማሸነፍ የጀመሩት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ በፓርከ ደ ፕሪንስ ይፋለማሉ።

ፓሪሰን ዠርማ የቻምፒየንስ ሊግ አጀማመሩ ድንቅ ቢሆንም በሊግ ኧ ግን ወጥ ብቃት ማሳየት አልቻለም።

ከመጨረሻዎቹ አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሦስቱን አቻ ተለያይቷል።

የበርካታ ተጫዋቾች ጉዳት እና ከባለፈው ዓመት አድካሚ የውድድር ዓመት በኋላ በቂ እረፍት አለማግኘቱ ወጥ ብቃት እንዳያሳይ ዋነኞቹ ምክንያት ናቸው።

ሙኒክ የውድድር ዓመቱ ጅማሮው እንከን አልባ ነው። በሁሉም ውድድር 15 ጨዋታዎችን አከናውኖ አንድም ነጥብ አልጣለም።

የቪንሰንት ኮምፓኒው ቡድን ተጋጣሚዎቹን በአሳማኝ ብቃት እያሸነፈ ቀጥሏል።

የጀርመኑ ክለብ ዛሬ ከ ፓሪሰን ዠርማ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ግን ቀላል ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም።

ሁለቱ ክለቦች በ2020 የቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተጫውተው ባየርን ሙኒክ 1ለ0 አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።

በአጠቃላይ 14 ጊዜ ተገናኝተው ሙኒክ ስምንት ፓሪሰን ዠርማ ደግሞ ስድስት ጨዋታ አሸንፈዋል።

የዛሬ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ጅማሮውን ያደርጋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review