ከውጭ የሚገቡ የቡና ማሽኖችን በሃገር ውስጥ ማምረት የቻለዉ ሥራ ፈጣሪ

You are currently viewing ከውጭ የሚገቡ የቡና ማሽኖችን በሃገር ውስጥ ማምረት የቻለዉ ሥራ ፈጣሪ

AMN – ጥቅምት 27 /2018 ዓ.ም

ዮናስ ሸዋንግዛው ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ኦሎምፒያ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር ምኞቱ እንደሆነ ይናገራል።

ለዓመታት በብረታ ብረትና ብየዳ ስራ ተሰማርቶ አሁንም ድረስ እየሰራ ይገኛል፡፡

የዓመታት የብረታ ብረት ስራዎች ከመስኮትና በር አለፍ ሲልም ከተለመዱ የቤትና የቢሮ ስራዎች የዘለለ አለመሆን ያላስደሰተዉ ዮናስ፣ ከዚህ የተለመደ አሰራር መውጣትን አዘውትሮ ይመኝ ነበር፡፡

ድርጅቱ ዮናስ ሶሊሽን ይባላል፡፡

ይህንን ያልኩት እኔ የምሰራው ሂደትን አይደለም መፍትሄን ነው፤ ለዚህ ደግሞ ትክክለኛውን ስያሜ ያገኘሁ ይመስለኛል የሚለው ዮናስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጠው ጎሮ ወጂ የኢንዱስትሪ መንደር በሚገኝ ሼድ ውስጥ የእሱን ሃሳብ የተከተሉ ከ25 የሚበልጡ ሰራተኞቹ ጋር ከሃገር አልፎ ዓለም ድረስ ዘልቆ ሃገርን ያስጠራ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ለገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዶላር ገቢ የምታገኝበት የግብርና ምርት የኢኮኖሚያችን ዋልታ የሆነው ቡና በስፋት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ትልቁ ችግር ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ባለቤት ባለመሆናቸው ነው የሚለው ዮናስ፣ ይህንን ችግር ሰምቶ እና አይቶ ዝም ማለት የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል ይላል፡፡

ስለሆነም ይህንን ደጋግሜ በማሰብ ወደ ስራ ገባሁ፤ ተሳካልኝም፡፡ አሁን ላይ ከውጭ የሚገባውን የቡና ማሽን መንግስት በሰጠኝ በዚህ መስሪያ ሼድ ውስጥ አምርቼ በስፋት ለቡና አምራች አርሶ አደሮች እያቀረብኩ ነው ሲል ተናግሯል።

በሰራው የቡና ማሽን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና እንደተቸረው ያወጋን ዮናስ፣ ለስራዎቹ በርካታ የምስክር ወረቀት እና የዋንጫ ሽልማት እንደተበረከተለት በማምረቻ ስፍራ ተገኝተን በዓይን ለማየት ችለናል፡፡

ሆኖም ግን የገበያ ትስስር ለመፍጠር መንግስት ባመቻቸለት ዕድል ወደ ሃገረ አንጎላ ጭምር ጥሪ ተደርጎለት በቦታው መገኘቱን የነገረን ዮናስ ሽዋንግዛው፣ አሁን ላይ መስራት ከቻልን አይኖች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ናቸው ሲል ተናግሯል፡፡

በዋናነት የተለያዩ የቡና ማሽኖችን እያመረትኩ እገኛለሁ የሚለው ዮናስ፣ ነገር ግን የማምረቻ ቦታ ጥበት ችግር እንደለበት ነው የተናገረው ፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review