5ኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ጥሩ አጀማመር ያደረገው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጌሌ አርሲን 9 ሰዓት ላይ ይገጥማል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአራት ጨዋታ 10 ነጥብ ሰብስቦ ከመሪዎቹ ክለቦች አንዱ ሲሆን ነጌሌ አርሲ በተመሳሳይ ጨዋታ ሁለት ነጥብ ይዟል።
በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ወላይታ ድቻ ከመቀለ 70 እንደርታ ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች ባደረጓቸው አራት አራት ጨዋታ ምንም አይነት ድል አላስመዘገቡም።
ከአሰልጣኙ ጋር መለያየቱ እንደማይቀር እየተነገረ የሚገኘው ወላይታ ድቻ አራቱንም ጨዋታ ተሸንፏል።
መቀለ 70 እንደርታም ከአራት ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ይዟል።
ጨዋታው ቀን 10 ሰዓት ላይ ይጀምራል።
በሸዋንግዛው ግርማ