የመደመር መንግስት በቴክኖሎጂ፤ በከተማ እና በገጠር ልማት ዘርፍ እያካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚያስችል ነዉ

You are currently viewing የመደመር መንግስት በቴክኖሎጂ፤ በከተማ እና በገጠር ልማት ዘርፍ እያካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚያስችል ነዉ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም

የመደመር መንግስት በተለይ በቴክኖሎጂ ፤ በከተማ እና በገጠር ልማት ዘርፍ እያካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሀገር ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚያስችል ነዉ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በአዳማ ከተማ የነበረው ስልጠና ዋና መሪ ሀሳቡ የመደመር መንግስት ላይ ያሉ የዘርፎች እመርታን ማየት ነው ብለዋል፡፡

የመደመር መንግስት አሁን እያካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አንፃር በግብርናው፣ በኢንዱስትሪው፣ በከተማ ልማቱ እና በገጠር ልማትም ጭምር ሰፊ ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡

በቃል ስንነጋገር የነበረውን ከዚህም በፊት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉትን ሥራዎች በአካል ተገኝቶ መጎብኘትም ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህም አንፃር የተነጋገርንባቸው ነገሮች በተግባር ምን ይመስላሉ፣ በዘርፎችስ ምን እምርታዎች አይተናል የሚለውን ከትናንት ጀምሮ ምልከታ እየተካሄደ እንደሚገኝም ነው የጠቆሙት፡፡

በትናንትናው ዕለትም የገጠር አካባቢን ከማበልጸግ አኳያም ምን የተሰሩ ስራዎች አሉ የሚለውን መመልከታቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የገጠር ልማትን ከግብርና ልማት ጋር የማስተሳሰር ሁኔታዎችን ማየታቸውን በመግለጽ፣ በሳይንስ ሙዚየም በመገኘትም ቴክኖሎጂን ለሀገር ልማት እንዴት መጠቀም እንችላለን የሚለውንም ማየት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ ዘመኑ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመሆኑ በዘርፉ በኢትዮጵያም ምን ተግባራት ተከናውነዋል የሚለውን ማየት ችለናል ብለዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review