7ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ በይፋ ተከፍቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚወሉ መሬቶችን በጨረታ አወዳድሮ ያስተላልፋል፡፡
ቢሮው በ7ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች 274 ፕሎቶች ወይም ቦታዎች መዘጋጀታቸውን አስታውቋል፡፡
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ፤ ከ5ሺህ በላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በበይነ መረብ ገዝተዋል ብለዋል፡፡
በዚህ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም 7 ካሬ ሜትር መሬት ለጨረታ መቅረቡንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
የመሬት ሊዝ ጨረታው ለ 5 ቀናት እንደሚቆይ የተናገሩት የቢሮው ኃላፊ፣ በዛሬው እለት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ጨረታ የወጣባቸው ቦታዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በሂደቱ ለሚነሱ ማንኛውም ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ኮሚቴ ስለመኖሩ አብራርተዋል፡፡
በቤተልሔም አየነው