አትሌቶች በቡድን ከተዘጋጁና የትራክ እጥረቱ ከተቀረፈ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተናገረች

You are currently viewing አትሌቶች በቡድን ከተዘጋጁና የትራክ እጥረቱ ከተቀረፈ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተናገረች

AMN-ህዳር 01/2018 ዓ.ም

በኦሊምፒክ ሦስት እንዲሁም በዓለም ሻምፒዮና አምስት በሁለቱ ውድድሮች ብቻ በድምሩ ስምንት የወርቅን ጨምሮ በርካታ የብርና የነሀስ ሜዳሊያዎችን ለሀገሯ ያስገኘችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

በሐገር አቋራጭ ውድድርም ቢሆን አምስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈችው ጥሩነሽ ትናንት በተካሄደው 43ኛው የሐገር አቋራጭ ውድድር ላይ ተገኝታ ተሳታፊ አትሌቶችን አበረታታለች፡፡

እነርሱ ውጤታማ የሁነት በጋራ በመስራታቸው መሆኑን የተናገረችው ጥሩነሽ፣ እንደ ቀድሞ አትሌቶች በቡድን መዘጋጀት ከተቻለ በዓለም ዓቀፍ መድረኮች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ብላለች፡፡

‹‹የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሌላኛው ችግር የማዘውተሪያ ስፍራ እጥረት ነው›› ትላለች በአንድ ኦሊምፒክ በሁለት ርቀቶች ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፡፡

መንግስትና የሚመለከተው ሁሉ የትራክ ችግሩን መቅረፍ ከቻሉ የኢትዮጵያን የቀድሞ የአትሌቲክስ ስኬት መመለስ እንደሚቻል ውጤታማዋ የቀድሞ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተናግራለች፡፡

የ40 ዓመቷ ጥሩነሽ ዲባባ ከትራክ ውድድር ራሷን ካገለለች በኋላ በ2017ቱ የለንደን ማራቶን የገባችበት 2:17:56 የዓለማችን የምንጊዜውም 16ኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review