የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ነገ ይጀምራሉ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ነገ ይጀምራሉ

‎AMN ህዳር 2/2018 ዓ.ም

‎በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክለው ክለብ የሚለይበት የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ላይ ደርሷል፡፡

‎የዚህ ዙር ጨዋታዎች ነገ ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ፣ ጅማና ሐዋሳ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡ በአዲስ አበባ ስታድዬም ነገ ረፋድ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ መድህን ጋር የሚደርጉት ጨዋታ የመዲናዋ መክፈቻ ነው፡፡ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በአርባ ምንጭ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ተጠባቂው ነው፡፡

‎ሐሙስ ሃድያ ሆሳዕና ከነጌሌ አርሲ፣ ባህርዳር ከተማ ከሸገር ከተማና አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና በዚሁ በአዲስ አበባ ስታድዬም የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡

‎ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ፣ መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ፣ ድሬደዋ ከተማ ከሐዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ምድረ ገነት ሽረ በሃዋሳ ከተማ ከሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች መካከል የሚጠበቁ ናቸው፡፡

‎በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review