AMN – ህዳር 03/2018 ዓ.ም
በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች አጀንዳ አሰባሰብ ነፃና ገለልተኛ በሆነ መንገድ እያከናወነ እንደሚገኝ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
በተለያዩ ጊዜያት ከመግባባት ያልተደረሰባቸው የህዝብ ጥያቄዎች በእስካሁኑ እንቅስቃሴው መታዘቡን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ ለAMN FM 96.3 ገልፀዋል።
በጉዳዩ ላይ አገር በቀል እውቀቶች ሲያገለግሉ ቢቆይም እንደ አገር ለሚፈጠሩ ሀገራዊና ፖለቲካዊ ችግርን በንግግርና በምክክር የመፍታት ባህላችን ግን ደካማ እንደነበር አቶ ጥበቡ ታደሠ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምክክር ችግራቸውን ከፈቱትም ካልተሳካላቸውም አገሮች ጥሩ ልምድ ማግኘታቸውን ያነሱት ቃለ አቀባዩ፣ የኢትዮጵያ ምክክር ሂደትም የተለየና ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ተግባራትንም እያከነዋነ መሆኑን አንስተዋል።
አጀንዳ የማሰባሰቡ ሂደት ታማኝነትና ግልፀኝነት እንዲኖረው የእስካሁኑ ክንውን ለመገናኛ ብዙሃን ግልፅ በማድረግ መሰራቱን ነው አቶ ጥበቡ ታደሰ የገለጹት፡፡
በሲሳይ ንብረቱ