የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከአባገዳዎች፣ ከሀደ ሲንቄዎች ጋር በሰላም እሴትና መቻቻል ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ ያለው ፋይዳ በሚል መሪ ሀሳብ ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ እንደገለጹት፣ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የመዲናዋ ሰላምና ፀጥታ ዘላቂና አስተማማኝ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ምክትል ቢሮ ሀላፊው ዘላቂ ሰላም በመገንባት ሂደቱ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና የጥበብ ባለሙያዎች የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይ የህዝቡን ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የመዲናዋን ሰላምና ፀጥታ ዘላቂና አስተማማኝ በሆነ መልኩ የማፅናት ስራ ከሁሉም ባለድርሻ ይጠበቃል ብለዋል።
የሰላም እሴቶትና መቻቻል ለሀገርና ትውልድ ግንባታ ያለው ፋይዳ ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ፅሁፍም ቀርቧል።
የመድረኩ ተሳታፊ የሀይማኖት አባቶች እና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች በበኩላቸው፣ የመዲናዋን ሰላም በመጠበቅና በልማት ስራዎች በመሳተፍ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ