“ስለ እናት ምድር” ፊልም አህጉራዊ ሽልማት አገኘ

You are currently viewing “ስለ እናት ምድር” ፊልም አህጉራዊ ሽልማት አገኘ

AMN ህዳር 4/2018

በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያተኮረው “ስለ እናት ምድር” (For Love, For Land, For power) ፊልም የአፍሪካ የፊልም አካዳሚ ሽልማትን አግኝቷል።

21ኛው የአፍሪካ የፊልም አካዳሚ ሽልማት (AMAA 2025) በናይጄሪያ ሌጎስ ተካሄዷል።

ትኩረቱን በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገው እና በዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ የተዘጋጀው “ስለ እናት ምድር” (For Love, For Land, For power) የተሰኘው ፊልም የዕይታ ጥበባት ውጤቶች (Visual Effects) ዘርፍ አሸንፏል።

ሽልማቱን የፊልሙ ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ ተቀብሏል።

በ2016 ዓ.ም የተመረቀው ፊልም በሀገር ፍቅርና በሰራዊቱ ህይወት ላይ ያተኮረ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት በተለይ በሰሜኑ ጦርነት ለአገር ሉአላዊነት መጠበቅ የከፈለውን አይተኬ ዋጋ የሚያሳይ ነው።

በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ በተዘጋጀው “ስለ እናት ምድር” ፊልም ላይ 30ሺ ሰዎች ተሳትፈውበታል።

መድረኩን የመራችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛና አዘጋጅ ቪምባይ ሙቲንሂሪ እኛ በቀኝ ካልተገዛችው ኢትዮጵያ የምንማረው ብዙ ጉዳይ አለን ብላለች።

ኢትዮጵያውን በራሳቸው የውስጥ አቅም የገነቡት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የራሳቸውን የሃይል ፍላጎት ማሟላት ችለዋል ያለችው ቪምባይ የዚህ ዓይነቱ ተሞክሮ ለናይጄሪያ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሳ እንኳን ደስ ያላችሁ ብላለች፡፡

“ስለ እናት ምድር” ሽልማት ከተሰጠባቸው 26 ዘርፎች በስምንቱ እጩ ሆኖ ቀርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review