የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸዉ 20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚከበርበት የአቢዮ ኤርሳሞ ስታድየም እና የክልሉ የተቋማት ህንፃ የግንባታ ሂደትን ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በተመስገን ይመር