ፈረንሳይ ለዓለም ዋንጫ ስታልፍ ፣ ፖርቹጋል ተሸንፋለች

You are currently viewing ፈረንሳይ ለዓለም ዋንጫ ስታልፍ ፣ ፖርቹጋል ተሸንፋለች

AMN – ህዳር 04/2018 ዓ/ም

በአውሮፓ ዞን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አራት ላይ የምትገኘው ፈረንሳይ ለውድድሩ ማለፏን አረጋግጣለች።

በፓርክ ደ ፕሪንስ ዩክሬንን ያስተናገደችው ፈረንሳይ 4ለ0 አሸንፋለች።

ኪሊያን እምባፔ በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስገኝ ማይክል ኦሊሴ እና ሁጎ ኢኪቲኬ ሌሎች ግቦችን አስቆጥረዋል።

ከአምስት የምድብ ጨዋታ 13 ነጥብ በመሰብሰብ ቀዳሚ መሆኗን ያረጋገጠችው ፈረንሳይ የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሆናለች።

በምድብ ስድስት የምትገኘው ፖርቹጋል ከሜዳዋ ውጪ በአየርላንድ 2ለ0 ተሸንፋለች።

ትሮይ ፓሮት ሁለቱንም የአየርላንድ ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በጨዋታው ተጫዋች የተማታው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

የ40 ዓመቱ የአል ናስር ኮከብ በእግርኳስ ህይወቱ የተመለከተው 13ኛ ቀይ ካርድ ሆኖም ተመዝግቧል።

ፖርቹጋል በቀጣይ በሜዳዋ አርሜኒያን ማሸነፍ በቀጥታ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ያደርጋታል።

በምድብ ዘጠኝ የምትገኘው ጣልያን በጂያንሉካ ማንቺኒ እና ፒዮ ኢስፖሲቶ ግቦች ሞልዶቫን 2ለ0 ማሸነፍ ችላለች።

ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው እንግሊዝ ሰርቢያን በዌምብሌይ አስተናግዳ 2ለ0 አሸንፋለች።

የአርሰናሎቹ ቡካዮ ሳካ እና ኤብሪቼ ኤዜ ሁለቱን ግቦች አስቆጥረዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review