ብሬኪንግ ረስት በሚል መጠሪያ የተለቀቀውና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤት የሆነው “ዎክ ማይ ዎክ” የተሰኘው ካንትሪ ስልት ሙዚቃ በአሜሪካ በሳምንቱ የሙዚቃ ሽያጭ ቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ከፍተኛውን ደረጃ መያዙ አነጋጋሪ ሆኗል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራው ሙዚቃ በጠንካራ የወንድ ድምፅ የተሰራ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል ሲሉ ኤ ቢ ሲ ኒውስን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ይገኛሉ፡፡
ሙዚቃው በሳምንቱ በዲጂታል ሽያጭ በአሜሪካ የካንትሪ (ሀገርኛ) ዜማዎች ዝነኛ እና ታዋቂ ከሆኑ የሙዚቀኛ ሥራዎች ጎራ ተመድቧል፡፡
ሙዚቃው እስከ አሁን በስፖቲፋይ 2.1 ሚሊዮን ጊዜ መደመጥ የቻለ ሲሆን፣ በዩቲዩብ ደግሞ 11.5 ሚሊዮን እይታዎችን አግኝቷል፡፡
ሆኖም ሙዚቃው በተለያዩ ሰዎች ዘንድ የሙዚቃ ባለሙያዎችን ስራና ተፈጥሮአዊ ጥበብ የሚያቃልል ከመሆኑም በተጨማሪ የኮፒ ራይት ጥያቄዎችንም የሚያስነሳ ነው በሚል በአስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ክርክርን አስነስቷል፡፡
በሊያት ካሳሁን