ከ28 ዓመት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ ለመመለስ የተቃረበችው ኖርዌይ ኢስቶኒያን 4ለ1 አሸንፋለች።
አሌክሳንደር ሶርሎዝ እና ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ኖርዌይ ሰባቱንም የምድብ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችላለች።
ምድብ ዘጠኝ ላይ የምትገኘው ኖርዌይ ከተከታይዋ ጣልያን በስድስት ነጥብ በልጣ ቀደሚነቱን ይዛለች።
ጣልያን ዛሬ ምሽት 4:45 ሞልዶቫን ትገጥማለች።
ኖርዌይ እና ጣልያን የፊታችን እሁድ እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ጣልያን የአንደኝነቱን ቦታ ተረክባ በቀጥታ ለማለፍ የዛሬ ምሽቱን የሞልዶቫን ጨዋታ ማሸነፍ እና እሀድ ኖርዌይን ከ10 በላይ ግብ አስቆጥራ መርታት ይጠበቅባታል።
በሸዋንግዛው ግርማ