በዩጋንዳ አንድ በመነፅር ሥራ ላይ የተሰማራ ድርጅት የወዳደቁ የከብት ቀንዶችን በመጠቀም ምቹና ተስማሚ የመነፅር ፍሬም ማምረቱ ተገልጿል፡፡
በዋና ከተማው ካማፓላ በየቀኑ በርከት ያለ እርድ የሚከናወን በመሆኑ የታረዱ ከብቶች ቀንዶች በስፋት ተጥለው ይገኛሉ፡፡ ይህን የተመለከተው ዋንዚ ቪዥን የተሰኘ ድርጅት በተለይም የላም ቀንዶችን በማሰባሰብ የፈጠራ ሥራውን ማከናወን መቻሉን የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የመነፅር ፍሬሞቹ ተስማሚ፣ ቆንጆና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ቆሻሻን ወደ ከፍተኛ ዋጋ ምርቶች በመለወጥ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና በዩጋንዳ የዓይን ሕክምናን ተደራሽ በማድረግ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሏል።
በማሬ ቃጦ