20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል እንደ ሀገር የተመዘገቡ ስኬቶችን በጋራ በማጣጣም ለቀጣይ ሀገራዊ ስኬቶች የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል

You are currently viewing 20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል እንደ ሀገር የተመዘገቡ ስኬቶችን በጋራ በማጣጣም ለቀጣይ ሀገራዊ ስኬቶች የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ህዳር 05/2018 ዓ.ም

20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል እንደ ሀገር የተመዘገቡ ስኬቶችን በጋራ በማጣጣም ለቀጣይ ሀገራዊ ስኬቶች የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል ሲሉ እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ከኢትዮጵያ መቻል እና ማንሰራራት በኋላ የሚከበረዉና የአብሮነት በዓል የሆነው 20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይከበራል፡፡

በዓሉ ከአመታት እንጉርጉሮ በኋላ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መመረቅን ተከትሎ፤ በነዳጅ በማዳበሪያ እና በኒውክለር ዘርፍም ሃገሪቱ በስኬት ጎዳና ላይ ባለችበት ሰዓት የሚከበር መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቶችን መጨረስ እና ለፍፃሜ ማብቃት ከለዉጡ አመታት ወዲህ ባህል እየሆነ መጥቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም የዚህ ትሩፋት ተጠቃሚ ነዉ ብለዋል፡፡

በ20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ላይ የሀገር ስኬቶችን በጋራ ማጣጣም ለቀጣይ ሀገራዊ ስኬትም የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review