በተለያየ መንገድ ለተገኘ የስራ ልምድና ክህሎት እውቅና መስጠት መቻሉ ኢንዱስትሪዎችንና ሰራተኞችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው

You are currently viewing በተለያየ መንገድ ለተገኘ የስራ ልምድና ክህሎት እውቅና መስጠት መቻሉ ኢንዱስትሪዎችንና ሰራተኞችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው

AMN – ህዳር 05/2018 ዓ.ም

በተለያየ መንገድ ለተገኘ የስራ ልምድና ክህሎት እውቅና መስጠት መቻሉ ኢንዲስትሪዎችና ሰራተኞቻቸውን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ትምሀርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ሀላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ፤ በተለይ ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ በሰጡት መረጃ፤ ባለስልጣኑ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በልምድ ለተገኙ ክህሎቶች ምዘና እና እውቅና መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል።

ልዩ ልዩ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ለማግኘት የአገልግሎት ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ አለልኝ፤ ስራው ከተጀመረ አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የልምድ ባለሙያዎች ምዘና ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ይህ እውቅና ባለሙያዎቹ በተሰማሩበት ሙያ ተወዳዳሪነታቸውን፣ ተፈላጊነትና ተመራጭነታቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳል የሚሉት ሀላፊው፤ ኢንደስትሪዎችም በባለሙያዎቻቸው ላይ እምነት በማሳደርና ምርታማነታቸውን በማሳደግ ውጤታማ ስራ ለማከናወን ያስችላቸዋልም ብለዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎችም ሆኑ ሌሎች ተቋማት በልምድ፣ እውቀትና ችሎታ ያገኙ ባለሙያዎቻቸውን አቅምና ችሎታ በማስመዘን ተቋማቸውንና ሰራተኞቻቸውን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ አቶ አለልኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review