የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛዉን የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በህብረ ብሔራዊነት ማሳያዉ የኢትዮጵያዊያን አብሮነት በሚያንፀባርቅ መልኩ ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ ተናገሩ፡፡
አፈ ጉባኤዋ በበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የፌደራሊዝም ስርዐት ማሳያ ሆኖ ባለፉት የለዉጥ አመታት ክልል ሆኖ የተደራጀዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዉስጡ ህብረ ብሄራዊነትን በተግባር የሚያሳይ መሆኑን የገለፁት አፈ ጉባኤዋ በዓሉ ሲከበር የኢትዮጵያ በልዩነት ዉስጥ የሚታይ ዉበት ለአለም የሚታይበት ነዉ ብለዋል፡፡
በዓሉን ለማክበር እና እንግዶችን በክብር ተቀቦሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸዉ ያሉም ሲሆን ለዚህም በትኩረት እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ባህል ትዉፊቶች መጋራት የክልሉን ፀጋዎችም ለሌሎች የማሳየት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር