በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ፋሮ አይስላንድን የገጠመችው ክሮሺያ 3ለ1 አሸንፋለች። በሜዳዋ የተጫወተችው ክሮሺያ የማሸነፊያ ግቦቹን በዮሽኮ ግቫርዲዮል ፣ ፔታር ሙሳ እና ኒኮላ ቭላሲች አማካኝነት አግኝታለች።
ምድብ 12 በበላይነት ያጠናቀቀችው ክሮሺያ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች። በምድብ ሰባት የተጠበቀው የፖላንድ እና ኔዘርላንድስ ጨዋታ 1ለ1 ተጠናቋል።
ጃኩብ ኪሚኒስኪ ለፖላንድ ፣ ሜምፊስ ዴፓይ ደግሞ ለኔዘርላንድስ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ጨዋታውን ብታሸንፍ ኖሮ የዓለም ዋንጫ ትኬቷን ታገኝ የነበረችው ኔዘርላንድስ በ17 ነጥብ ስትመራ ፣ ፖላንድ በ14 ትከተላለች።
በቀጣይ ኔዘርላንድስ በሜድዋ ሊቱኤንያን ስታስተናግድ ፣ ፖላንድ ማልታን ትገጥማለች። ምድብ አንድ ላይ የምትገኘው ጀርመን ሉግዘንበርግን 2ለ0 ረታለች።
የኒውካስትሉ አጥቂ ኒክ ቮልትማደ ሁለቱንም ግቦች በስሙ አስመዝግቧል። በዚሁ ምድብ ስሎቫኪያ በቶማስ ቦብቼክ ብቸኛ ግብ ሰሜን አየርላንድን 1ለ0 አሸንፋለች።
ጀርመን እና ስሎቫኪያ በእኩል 12 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው የመጀመሪያ ሁለቱን ደረጃዎች ይዘዋል። ሁለቱ ሀገራት የመጨረሻ የምድ ጨዋታቸውን የፊታችን ሰኞ በጀርመን ሩድ ቡል አሬና እርስ በእርስ ያከናውናሉ።
በሸዋንግዛው ግርማ