የአንገት ዲስክ መንሸራተት እንዴት ይከሰታል? ህክምናውስ ምን ይመስላል?

You are currently viewing የአንገት ዲስክ መንሸራተት እንዴት ይከሰታል? ህክምናውስ ምን ይመስላል?
  • Post category:ጤና

AMN – ህዳር 6/2018 ዓ.ም

‎የአንገት ዲስክ መንሸራተት በእድሜ እና በተለያዩ አደጋዎች ሊከሰት የሚችል ህመም እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

‎አንገት ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ሲንቀሳቀስ የመገጣጠሚያ ዲስኮች በየተወሰነ ድግሪ እጥፋት እየተቋቋሙ ወይም እየቻለ የዘወትር ስራውን እንደሚቀጥል ባለሞያዎች ይናገራሉ።

የአንገት ዲስክ ልክ እንደ ወገብ እና ጀርባ እርጅና ሊያጋጥመው እንደሚችል ፣በአደጋ ጊዜ ሊሰነጠቅ፣ ሊደክም እንደሚችል ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የቅዱስ ጰውሎስ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአንጎል እና ህብለ ሰረሰር የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶ/ር አናኒያ ጂንባይ ተናግረዋል።

‎ይህ በሚሆንበት ጊዜ ዲስክ ወደ ኋላ ወይም ወደ ጎን የመንሸራተት ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ወይም ሊያስከትል እንደሚችል ያስረዳሉ ። የአንገት ዲስክ እንደማንኛወም አከርካሪ አጥንት ከአንጎል ወደ ህብለ ሰረሰር የሚሄደው በአጥንት ተሸፍኖ መሆኑን ተናግረዋል ።

‎አጥንቶች መሀል ያለውን ዲስክ ለመንቀሳቀስ ደግሞ እንደ ጄል የመሰለ ፈሳሽ መገጣጠሚያዎች መሀል እንዳለ ገልፀዋል።

‎በአብዛኛው ጊዜ የሚያሰጋው የአንጎል ዲስክ ወደ ጎን አና ትንሽ ወደ ኋላ በሚንሸራተት ጊዜ የሚወጡ ነርቮች ሲታፈኑ መሆኑን ጠቁመዋል ።

‎አልፎ አልፎ ደግሞ የአንገት ዲስክ ወደ ኋላ በሚንሸራተትበት ጊዜ ዋናውን ህብለ ሰረሰር የመጫን ሁኔታ እንደሚኖር፣ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር የአንገት ዲስክ መንሸራተት ተፈጠረ የሚባለው የነርቭ ስራ ሲታወክ እንደሆነ ነው የገለፁት ።

‎የአንገት ላይ ህመም ብዙ መስኤዎች እንዳሉት፣ ከትራስ አለመመቸት ጀምሮ እስከ ትልቅ አደጋዎች ህመሙን ሊያስከትሉ ይችላሉ ሲሉ የህመሙን መንስኤ ይገልፃሉ ።

‎ከአንገት ህመም ጋር ተያይዞ እንዳለ ወደ እጅ የሚሰራጭ ህመም ሲኖር ፣መደንዘዝ ሲያጋጥም፣ አልፎ አልፎ መስነፍ እና መዛል በሚኖርበት ጊዜ የአንገት ዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

‎ከአንገት ተነስቶ ወደ እጅ አቅጣጫ የሚሄደው ህመም ስሜቱን ለመግለፅ አዳገች መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ ህመም የተያዙ ታካሚዎች የማሳከክ፣ የመቆጥቆጥ፣ እንደ ኤሌክትሪክ የመንዘር ስሜቶች እንደሚያስተናግዱ ተናግረዋል።

‎አንዳንዱ ደግሞ የማቃጠል ስሜት ሲኖር የአንገት ዲስክ መንሸራተት ሲያጋጥም የሚከሰት ምልክት መሆኑን ነው ያመላከቱት።

‎ሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ የሆኑ የህመም ምልክቶች እንደማያሳዩ አስረድተው፣ የትኛው ነርቭ ታፈነ፣ የትኛው ደረጃ ላይ ያለው ዲስክ ይበልጥ የተንሸራተተው እና ነርቩን የተጫነው በሚለው የተነሳ ስሜቶቹም የተለያዩ መሆናቸውን ይገልፃሉ።

‎የአንገት ዲስክ መንሸራተት በእድሜ የሚከሰትበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ፣ ከዚያ ውጭ ለሰዓታት ስልክ ላይ አቀርቅሮ መጠቀሙ አንገት ፍሌክል የተባለውን ቁመና ሲይዝ ዲስኩን ትልቅ ጫና ስለሚፈጥርበት የመድከም እና የመዛል ሁኔታዎች ይፈጥራል ብለዋል ።

‎የአንገት ዲስክ ህመም እንዴት ይታከማል?

‎የአንገት ዲስክ መንሸራተት ህክምና በሶስት ይከፍሉታል።

‎አንደኛው ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት በራሱ የመቀነስ እና የመጥፋት ሁኔታ ሲኖረው በቀላሉ ሊድን የሚችል አይነት በመሆኑ በራሱ ግዜ ወደ ነበረበት እንደሚመለስ ተናግረዋል።

‎የአንገት ዲስክ መንሸራተት ሆኖ በራሱ ጊዜ የማይተው እና ህመም ሲኖር ደግሞ ተከታታይ የሜዲካል ህክምና ሊታከም እንደሚችል ነው የተናገሩት።

‎ሁለተኛው በዚሁ ሜዲካል ህክምና ውስጥ የሚታዘዙ መድሀኒቶችን በመስጠት እንደሚታከም ገልፀው፣ ከዚህ በተጨማሪ የአንገት ፊዝዮ ቴራፒ ስፖርቶችን እንዲጀምሩ ይደረጋል ብለዋል ።

‎ይህ ህክምና የአንገት ዲስክ ያለበት ጫና መሰረት ተደርጎ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል ።

‎ሶስተኛው የአንገት ዲስክ መንሸራተት ህመም በቀዶ ጥገና የሚሰጥ ህክምና መሆኑን ተናግረዋል።

‎ የአንገት ዲስክ መንሸራተት እንዴት ቀድሞ መከላከል ይቻላል?

‎የአንገት ዲስክ መንሸራተት መከላከል የሚቻልባቸው ዘዴዎች እንዳሉ ይገልፃሉ።

‎አንደኛውና ዋነኛው ለረዥም ሰዓት አቀርቅሮ ስልክ ባለመጠቀም ቀድሞ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

‎እየተንቀሳቀሱ በመስራት ችግሮቹ እንዳይከሰቱ ማድረግ ይቻላል በማለት ይመክራሉ።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review