ኢትዮጰያ የተከሰተውን የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው

You are currently viewing ኢትዮጰያ የተከሰተውን የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው
  • Post category:ጤና

‎AMN ህዳር 5/2018 ዓ.ም

‎የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡

‎ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት መቻሉን መግለፁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በደቡብ ኢትዮጰያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

‎ዋና ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገፆቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ ኢትዮጰያ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል 9 ሰዎች ያጠቃውን በሽታ የማርበርግ ቫይረስ መሆኑን ማረጋገጧን ገልፀዋል።

‎ በኢትዮጰያ የተከሰተውን በሽታ ፈጣንእና ግልፅ ምላሽ ለመስጠት የጤና ሚንስቴር፣የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ጤና ኢንልቲትዮት እና የክልሉ የጤና ቢሮ ያደረጉትን ጥረት ዋና ዳይሬክተሩ አድንቀዋል።

‎ይህ እርምጃ ኢትዮጰያ ወረርሽኑ በፍጥነት ለመቆጣጠር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አድናቆታቸውን ባሰፈሩት መልክት ገልፀዋል።

‎የአለም የጤና ድርጅት በየደረጃው ባሉ ቅርጫፎቹ በሽታውን ለመቆጣጠር እና የተያዙ ሰዎችን ለማከም በንቃት እየደገፈ መሆኑን ገልፀው፣ ድንበር ተሻጋሪ ስርጭትን ለመቋቋም የሚደረገውን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በሄለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review