በከተማዋ ሰላምና ፀጥታን የማፅናት ተልዕኮ ላይ የተሰማሩ አደረጃጀቶችን በማቀናጀት የተጀመረው ማሕበረሰቡን የሰላሙ ባለቤት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተለያዩ የፀጥታ አደረጃጀቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ ዛሬ ላይ አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ሁሉን አቀፍና አካታች ለውጥ ግቡን እንዲመታ በፀጥታ መዋቅሩ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት ሰላምን የማፅናት ሚና ላቅ ያለ መሆኑን አንስተዋል።

ሰላምን ማፅናት የአንድ ጀምበር ተልዕኮ ብቻ ባለመሆኑ ሁሌም ዝግጁ መሆንን ይጠይቃል ያሉት አቶ ፍሰሃ አያይዘውም የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማፅናት በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም የከተማዋን ማሕበረሰብ የሰላሙ ባለቤትነቱን ይበልጥ በማጠናከር ሕግ የማስከበር ተልዕኮቻችንን ሁሌም በስኬት ልንወጣ ይገባል ሲሉም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ማሕበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አመራሮች፣ የአስራ አንዱም ከረፍለ ከተሞች የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት የተወከሉ አባላት እንዲሁም ከቅጥር ጥበቃ የተውጣጡ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በተልዕኳቸው ላይ ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ያጋሩ ሲሆን ያጋጠሙዋቸውን ችግሮችን በማንሳት በመፍትሄዎቿቸው ዙሪያ መክረዋል።
በ ታምሩ ደምሴ