ለዋንጫ የምትጠበቀው ኢትዮጵያ ውድድሯን ዛሬ ትጀምራለች

You are currently viewing ለዋንጫ የምትጠበቀው ኢትዮጵያ ውድድሯን ዛሬ ትጀምራለች

AMN – ህዳር 06/2018 ዓ/ም

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት(ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል።

ኢትዮጵያ የምታሰናዳው ውድድር 10 ሀገራት ይሳተፉበታል።

በምድብ አንድ የተደለደሉ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲሁም በምድብ ሁለት የሚገኙ ሀገራት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ለዋንጫ የምትጠበቀው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም 10 ሰዓት ላይ ከሩዋንዳ ጋር ታደርጋለች።

ከዚህ ጨዋታ ቀድም ብሎ ቀን 7 ሰዓት ሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን ይጫወታሉ።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች ሲከናወኑ 11 ሰዓት ላይ ታንዛኒያ ከሱዳን ፣ ምሽት 2 ሰዓት ብሩንዲ ከዩጋንዳ የሚጫወቱ ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review