አዲስ የተሻሻለው የህንፃ ግንባታ እና ተያያዥ መመሪያ ከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የህንፃ ግንባታ እንዲኖራት ይረዳል

You are currently viewing አዲስ የተሻሻለው የህንፃ ግንባታ እና ተያያዥ መመሪያ ከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የህንፃ ግንባታ እንዲኖራት ይረዳል

AMN- ህዳር 6/2018 ዓ.ም

አዲስ የተሻሻለው ህንፃዎች ከመንገድ ስለሚኖራቸው ርቀት፣ የፕላኒንግ የመሬት ልማት እና ተያያዥ መመሪያ ከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የህንፃ ግንባታ እንዲኖራት እንደሚረዳ ተመላከተ።

አዲስ በተሻሻለው ህንፃዎች ከመንገድ ስለሚኖራቸው ርቀት፣ የፕላኒንግ፣ የመሬት ልማት እና ተያያዥ መመሪያዎች ላይ ባለድርሻ አካላት የተገኙበት ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ከአዲስ አበባ ፕላን እና ልማት ቢሮ፣ ከግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም ከመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመጡ ባለሙያዎች ማብራርያ ይሰጣሉ።

መርሐ-ግብሩ በወጡት ህጎች ዙርያ ግንዛቤ መፍጠር፣ መሻሻል ይገባቸዋል የተባሉ ነጥቦች ላይ መወያየት እንዲሁም ከዚህ በኋላ ለሚወጡ ህጎች ግብአት የሚሆን ሀሳብ ማቅረብ መቻል መሆኑ ተገልጿል።

ባለድርሻ አካላቱ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ መድረኩን ያመቻቸው የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ መሰል መርሐ-ግብሮች ግንዛቤን በማስረፅ ለመመሪያዎች ተፈፃሚነት እና ከተማዋ ለጀመረችው የልማት ስራ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብሏል።

በቤተልሔም አየነው እና ሰላም ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review