ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት ሚናቸውን እንዲወጡ የተጀመሩ ፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ማላቅ ይገባል

You are currently viewing ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት ሚናቸውን እንዲወጡ የተጀመሩ ፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ማላቅ ይገባል

AMN- ህዳር 6/2018 ዓ.ም

ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት ሚናቸውን እንዲወጡ የተጀመሩ ፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ማላቅ እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራስ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ 10ኛውን የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ከፍተዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ከተሜነትን የብልጽግና መዳረሻ ማድረግ አንዱ እሳቤ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ የተቀናጀ የከተማ ልማት እሳቤ በመተግበር ከተሞች ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚፈጠርባቸውና የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

የከተሞች ፎረምም የከተማ ለከተማ ትስስርን በመፍጠር ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታት ፋይዳው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

የከተሞች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም፣ መድረስ ካለባቸው እድገት አንጻር ብዙ ስራዎች ይጠበቅባቸዋል ያሉት አቶ አደም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ በተደረጉ እሳቤዎች ብሩህ ተስፋን የፈነጠቁ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማትም በ73 ከተሞች ተስፋፍቶ የከተሞችን ጽዳትና ደረጃ ማሻሻሉን ነው የገለጹት።

በከተሞች አሁንም የከተማ ልማት አገልግሎትን ፈጣን ማድረግ፣ ከተሞችን በብቁ ፕላን መምራት፣ የቤት አቅርቦትን ማስፋት፣ መሰረተ ልማት ግንባታን በፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ማዝለቅ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማስፋት እና የኑሮ ውድነትን ማቅለል ትኩረት የሚሹ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review