ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር አዘጋጅ ኢትዮጵያ ሩዋንዳን አሸንፋለች።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ 2ለ0 ማሸነፍ ችላለች።
ዳዊት ካሳው እና ሁዘይፋ ሻፊ የማሸነፊያ ግቦችን በስማቸው አስመዝግበዋል።
ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምድብ አንድን መምራት ጀምራለች።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ቡድን በቀጣይ ማክሰኞ ደቡብ ሱዳንን ይገጥማል።
በሸዋንግዛው ግርማ