ከቦሌ ሚካኤል ወደ ጎርጎሪዎስ ቤተ-ክርስቲያን አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

You are currently viewing ከቦሌ ሚካኤል ወደ ጎርጎሪዎስ ቤተ-ክርስቲያን አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

AMN ህዳር 6 ቀን 2018

ከጎርጎሪዎስ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው ድልድይ ላይ ያጋጠመውን መቦርቦር ለማስተካከል ለትራፊክ ዝግ የነበረው መንገድ የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

የጥገና ሥራው የተጎዳውን የድልድይ ክፍል በኮንክሪት መሙላት እንዲሁም ከጎርጎሪዎስ አደባባይ እስከ ቦሌ ሚካኤል መስቀለኛ ድረስ አልፎ አልፎ የተቦረቦረውን የመንገዱን የአስፋልት ክፍል የመጠገን ስራ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ የጥገና ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መንገዱ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ባለስልጣኑ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review