የተፈጥሮ ለዛ እና ስነ-ምህዳር ሳይርቃቸዉ ከተሜነትን ያቀፋ አካባቢዎችን ለመፍጠር እየተሰራ ነው

You are currently viewing የተፈጥሮ ለዛ እና ስነ-ምህዳር ሳይርቃቸዉ ከተሜነትን ያቀፋ አካባቢዎችን ለመፍጠር እየተሰራ ነው

AMN – ህዳር 7/2018 ዓ.ም

የተፈጥሮ ለዛ እና ስነ-ምህዳር ሳይርቃቸዉ ከተሜነትን ያቀፋ አካባቢዎችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በገጠር ኮሪደር ስራ መሰረተ ልማቶችን ማስፋት እና የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻል ላይ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ በጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ የተገነቡ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮችን ጎብኝተዋል፡፡

መንግስት ከተማን እና ከተሜነትን በማስፋት አንድም የዜጎችን አኗኗር ማዘመን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት ላይ የሚሰራቸዉ ስራዎች ውጤታማነቱ በተግባር እየታየ ነው ብለዋል፡፡

መሰረተ ልማትን መዘርጋት እና ከተማን ከገጠር በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር ላይም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዉ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው በገጠር ሁሉን ያሟላ አኗኗር በመንግስት መፈጠሩ ደስታን እንደፈጠረላቸዉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም መሰል የዜጎችን አኗኗር የሚያሻሽሉ ኢኮኖሚውንም የሚያነቃቁ ስራዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡፡

በተመስገን ይመር

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ምርጫዎ ያድርጉ ! የትዉልድ ድምጽ ! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addismedianetwork

#VoiceOfGenerations

#Ethiopia

#addisababa

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review