እንግሊዝ ምንም ግብ ሳይቆጠርባት ማጣሪያዋን አጠናቀቀች

You are currently viewing እንግሊዝ ምንም ግብ ሳይቆጠርባት ማጣሪያዋን አጠናቀቀች

AMN – ህዳር 07/2018 ዓ/ም

ቀድማ ለዓለም ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠችው እንግሊዝ በመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዋ አልባንያን 2ለ0 አሸንፋለች። የባየርን ሙኒኩ አጥቂ ሀሪ ኬን የሁለቱም ግቦች ባለቤት ሆኗል።

በምድብ 11 የተደለደለችው እንግሊዝ ያደረገቻቸውን ስምንቱንም ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርባት ማሸነፍ ችላለች። አልባንያ ሽንፈት ቢገጥማትም 2ኛ ሆና አጠናቃለች።

በዚሁ ምድብ ሰርቢያ ላቲቪያን 2ለ1 በመርታት 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በምድብ አራት ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ፈረንሳይ አዘርባይጃን 3ለ1 ስታሸንፍ ፣ ዩክሬን አይስላንድን 2ለ0 ረታለች። ዩክሬን ፈረንሳይን ተከትላ በማጠናቀቋ በጥሎ ማለፍ ዙር የምትሳተፍ ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review