በአገልግሎት ዘርፍ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመቀነስና አገልግሎትን አሰጣጥን ለማዘመን በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅጣጫ ሰጨነት በፌደራል ደረጃ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሎች እየተስፋፋ ይገኛል።
ሁሉም ክልሎች ለነዋሪዎቻቸው ዲጂታል የሆነ አሰራርን ተደራሽ በማድረግ እንግልትን ለመቀነስና ጊዜን ለመቆጠብ ተመራጭ እየሆነ መጥቷል አገልግሎቱ።
የአፋር ክልልም በሰመራ ከተማ መሶብ (ኮራ) የአንድ ማዕከልን ወደ አገልግሎት አስገብቷል።
በማዕከሉ 5 ተቋማት13 አገልግሎቶችን እንደሚሰጡ የማዕከሉ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ከሊል አሊ ለኤኤምኤን ተናግረዋል።
ክልሉ በቀጣይም ተጨማሪ ግንባታዎችን በማከናወን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ 100 ለማድረስ ማቀዱን ኃላፊው ነግረውናል።
አገልግሎቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌደራል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አስጀምረዋል።
በፍቃዱ መለሰ