በአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ምቹ የሆነ የስራ አካባቢ መፈጠር ሕዝቡን በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል ያግዛል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር ) ገለጹ
የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊዎች በልደታ ክፍለ ከተማ የተከናነው ምቹ የስራ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል።
የመንግስት ሰራተኛች በመስሪያ ቦታቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ግብአት እንዲያገኙ መደረጉ፤ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ማሳያ መሆኑ እና ይህም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር ) አንስተዋል ።
በአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ምቹ የሆነ የስራ አካባቢ መፈጠር ሕዝቡን በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል እንደሚያግዝ የቢሮዉ ኃላፊ ገልጸዋል ።
የክፍለ ከተማው የመንግስት ሰራተኞችም በመስሪያ ቦታችን ምቹ የስራ አካባቢ መፈጠሩ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ።
በመስሪያ ቦታችን የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶች መገኘታቸው ከዋጋ ባሻገር አላስፈላጊ እንግልትን ያስቀርልናልም ብለዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ልዕልቲ ግደይ በክፍለ ከተማዉ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ ስኬቶች ላይ የሰራተኞች ሚና የላቀ መሆኑን ጠቅሰዉ ሰራተኞች ጤናቸውን ጠብቀው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት መስሪያ ጂም ተሟልቷል ብለዋል።
በሆቴል ክራይ የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመቀነስ የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የሰራተኞች ክበብ አገልግሎት መጀመሩንም ገልጸዋል ።
በአጠቃላይ በክፍለ ከተማው የሰራተኞች ክበብ ፣ ሱፐር ማርኬት ፣ የሕጻናት ማቆያ መጫወቻ ፣ የሕክምና መስጫ ፣ የስልጣን ማዕከል ፣ ጂም ፣ ቤተ መጻህፍት ፣ የተገልጋይ ማረፊያ እና ሌሎች ምቹ የስራ አካባቢ ተፈጥሯል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ።
ክፍለ ከተማው ስታንዳርዱን የጠበቀ የወረፋ ማስጠበቂያ፣ የውስጥና የውጭ ካሜራ መቆጣጠሪያ ሴንተር ፣ዲስፕሌዮች፣ ዲጅታል ዙም ሚቲንግ ፣ QR ኮድ ያለው የሰራተኞች ባጅና ሌሎችንም ስራ አስጀምሯል።
በዳንኤል መላኩ