ይህ ተፈጥሮን የመንከባከብ ጥበብ በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ቆጠር ገድራ ቀበሌ የሚገኝ ጥብቅ ደን ላይ ይገለጣል፡፡
በአካባቢዉ ህብረተሰብ ነባር ባህል መሰረት፣ የጥንት አባቶች የጠበቀ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡
“ጉርዳ” ተፈጥሮን የመንከባከብ ልዩ ጥበብ ነዉ፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ዛፍ ላለመቁረጥ እና ዛፍን ተንከባክቦ ሊያሳድግ ቃል ኪዳን አለው፡፡
የቆጠር ገድራ ደን በውስጡ አብያተ ክርስቲያናትን እና በርካታ እምቅ ሀብቶችን ይዟል፡፡
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሚከበርበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያሉትን ፀጋዎች ለመገናኛ ብዙሃን እያስጎበኘ ነው፡፡
በተመስገን ይመር