የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ መሸጥ መከልከሉን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በተለይ ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ አሳውቋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ፣ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ሳሙና እና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ ባለመሆኑ ለመከልከል መገደዳቸውን ተናግረዋል።
እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑንም አስረድተዋል።
ሕብረተሰቡ ለጤናው ጠንቅ መሆኑን ተገንዝቦ ተባባሪ እንዲሆንና ጥቆማም እንዲሰጥ የጠየቁት ምክትል ሥራ አስኪያጁ፣ ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎችም ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስገንዝበዋል።
በሲሳይ ንብረቱ