ብዙዎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በአንድ ጀምበር በሚል ክፍለ ከተሞች ያደረጉት ርብርብ አበረታች ውጤት አስገኝቷል

You are currently viewing ብዙዎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በአንድ ጀምበር በሚል ክፍለ ከተሞች ያደረጉት ርብርብ አበረታች ውጤት አስገኝቷል

AMN- ህዳር 8/2018 ዓ.ም

ብዙዎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በአንድ ጀምበር በሚል ክፍለ ከተሞች ያደረጉት ርብርብ አበረታች ውጤት ማስገኘቱን የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የ4ወር እና የአንድ ጀምበር የስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የፀጋ ልየታ የንቅናቄ ስራዎችን አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ የንቅናቄው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

በውይይቱ ላይ ብዙዎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በአንድ ጀምበር በሚል ክ/ከተሞች ያደረጉት ርብርብ አበረታች ውጤት ማስገኘቱን የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ጠቅሰዋል፡፡

የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም መልካም የሚባል ቢሆንም፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ፍትሀዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የከተማዋን ነዋሪዎች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ሞገስ፣ ከሴቶች ተጠቃሚነት አንፃር እየመጣ ያለው መሻሻል በወጣቶች እንዲሁም በአዳዲስ ምሩቃንም የላቀ ለውጥ እንዲመጣ የአመለካከት ችግርን ጨምሮ ሌሎች ውስንነቶችን መቅረፍ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነት ከፍ ማለት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ጉዞ የላቀ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰው፣ የንቅናቄ ስራዎችን በፓርቲ አስተባባሪነት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስራን የማማረጥ እና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለሚያረጋግጡ ዘርፎች ትኩረት ያለመስጠትን የአመለካከት ችግር በስልጠና እያረሙ መጓዝ እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ከብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው፣ የስራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ስራዎች ዕቅዶችን ማሳካት የሚችሉ አበረታች ጅምሮች ቢኖሩም፣ በተለዩ ፀጋዎች ላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማነቆዎችን ማስወገድ እንደሚገባ ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review