ማንችስተር ዩናይትድ የቅርጫት ኳስ ቡድን ሊመሰርት ነው

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ የቅርጫት ኳስ ቡድን ሊመሰርት ነው

AMN-ህዳር 9/2018 ዓ.ም

ማንችስተር ዩናይትድ የቅርጫት ኳስ ቡድን ለመመስረት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተዘግቧል።

የእንግሊዙ ክለብ ከፊል ባለድርሻ ሰር ጂም ራትክሊፍ የክለቡን እውቅና ተጠቅመው ተጨማሪ ገቢ የማግኛ መንገዶችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

በአሜሪካ በደንብ መሰረቱን የጣለው እና በአውሮፓ ተወዳጅነቱ እየሰፋ የመጣው የቅርጫት ኳስ ስፖርት እሳት የላሱ ነጋዴ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሰርጂም ራትክሊፍ ትኩረትን ሆኗል።

የጣልያን ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጂአኒ ፔትሩቺ ከኮሬር ዴሎ ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ ስፖርቱን በአውሮፓ ለማስፋፋት ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ፔትሩቺ እስከ 50 ቢሊየን ዶላር የገቢያ አቅም ባለው የቅርጫት ኳስ ስፖርት ላይ አውሮፓ ያለው ድርሻ የ200 ሚሊየን ዶላር ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

ተወዳጅነቱ እየሰፋ ከመጣው ከዚህ ስፖርት ገቢ ተቋዳሽ ለመሆን አህጉር አቀፍ ኤን ቢ ኤ ዩሮፕ (NBA Europe) ሊግ የመመስረት እቅድ እንዳለ ጂአኒ ፔትሩቺ ተናግረዋል።

በአውሮፓ “ዩሮ ሊግ” የተሰኘ አህጉራዊ የቅርጫት ኳስ ውድድር ቢኖርም ፔትሩቺ እና አጋሮቻቸው የበለጠ ገንዘብ ማስገኘት የሚችል አዲስ ሊግ ለመመስረት ውጥን ላይ ናቸው።

እንደ ማንችስተር ዩናይትድ አይነት ጉዙፍ እና ዓለማቀፋዊነቱ የናኘ ክለብ በዚህ ሊግ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቱ ስፖርቱ አዋጭ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ገና በንግግር ላይ የሚገኘው “ኤን ቢ ኤ ዩሮፕ” የመመስረት ሂደት እውን ከሆነ ታላላቅ የአውሮፓ ከተሞች ደረጃው ከፍ ያለ የቅርጫት ኳስ ፉክክር ይታይባቸዋል ተብሏል።

ማንችስተር ዩናይትድም የዚህ አካል ለመሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን በርካታ የብዙሃን መገናኛ ተቀባብለው ዘግበውታል።

ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና የመሳሰሉ የእግርኳስ ሀያላን ክለቦች የቅርጫት ኳስ ቡድን ቢኖራቸውም የእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች ግን በዚህ ስፖርት ሲሳተፉ አይታይም።

በሸዋንግዛው ግርማ

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addismedianetwork

#Ethiopia

#addisababa

#Football

#manchesterunited

#basketballgame

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review