በተሟላ መንገድ መስራት ካልተቻለ በእግርኳሱ ለውጥ እንደማይመጣ ዳዊት እስጢፋኖስ ተናገረ

You are currently viewing በተሟላ መንገድ መስራት ካልተቻለ በእግርኳሱ ለውጥ እንደማይመጣ ዳዊት እስጢፋኖስ ተናገረ

AMN-ህዳር 9/2018 ዓ.ም

በቅርቡ የተመሰረተው የዳዊት እስጢፋኖስ እግር ኳስ ፕሮጀክት በተለያዩ የእድሜ እርከኖች እስከ 110 የሚደርሱ ሰልጣኞች ይዟል።

ሰልጣኞቹ እድሜያቸውን ያማከለ ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ እና ወደፊት ሀገርን የሚያስጠራ ስፖርተኛ ለመሆን እየሰሩ እንደሆነ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ አሰልጣኞች ታዳጊዎችን ለማፍራት ሳይንሳዊ የሆነ ስልጠና እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች እና የፕሮጀክቱ ባለቤት ዳዊት እስጢፋኖስ እግርኳሱን ለማሳደግ እንደ ሀገር በተሟላ መንገድ መስራት ካልተቻለ ለውጥ እንደማይመጣ ተናግሯል።

በየአካባቢው ያሉ የማዘውተሪያ ስፍራዎች አሁን ላይ በርካታ ታዳጊዎችን ለማፍራት ሚናቸው የጎላ ነው የሚለው አሰልጣኝ ዳዊት እግር ኳሱን ለማሳደግ ተጨማሪ ሜዳዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁሟል።

በአልማዝ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review