የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዳዊት ካሳውን አድንቀዋል።
አሰልጣኙ ደቡብ ሱዳንን 4ለ1 ካሸነፉ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቡድኑ ባሳየው እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“ጨዋታውን በምንፈልገው መንገድ ተቆጣጥረናል። ተጫዋቾቹ ባሳዩት ዲሲፕሊን ደስተኛ ነኝ።” ሲሉ ገልፀዋል።
በጨዋታው ሀትሪክ ስለሰራው ዳዊት ካሳው የተጠየቁት ቤንጃሚን ዚመር “ዳዊት የኢትዮጵያ ወርቃማ ልጅ የመሆን አቅም አለው። በርካታ ክህሎት ያለው ድንቅ ተጫዋች ነው። ጥሩ ስነምግባር ያለው እና ጠንክሮ የሚሰራ ተጫዋች በመሆኑ ለእርሱ ትልቅ አክብሮት አለኝ።” ሲሉ ገልፀውታል።
በሸዋንግዛው ግርማ