የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩትን ጎበኙ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩትን ጎበኙ

AMN ህዳር 9/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) ተመርቆ ክፍት የሆነውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩትን ጎብኝተዋል።

የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ማበልጸግ እና መጠቀም እንዲቻል በ2013 ዓ. ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተቋቋመው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ዛሬ በብዙ ተልዕኮ አድጎና ትላልቅ ሃገራዊ ስራዎችን መስራት በሚችል መልኩ ተደራጅቷል፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁሉንም ሴክተር የሚነካ በመሆኑ በተለይም በስማርት ከተማ ግንባታ ላይ ለምትገኘው አዲስ አበባ ቴክኖሎጂው የሚኖረው ሚና እጅግ የላቀ ነው።

ኢንስቲትዩቱ ከተሞችን ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ የስማርት ሲቲ ፕሮግራምን እያዘመነ ይገኛል፡፡

ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎትን በአንድ ማዕከል የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሶፍትዌር አበልጽጎም ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ኢንስቲቲዩቱ በኮምፒውተር ቪዥን፤ በማሽን ለርኒግ ፤ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና በቢግ ዳታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡

“አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለሁሉም“ ን መርህ አድርጎ እየሰራ ያለው ኢንስቲቲዩቱ ለምርምርና ልማት የሚያስፈልገውን ግዙፍ ዳታ ላይ የተመሰረተ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለሃገራዊ ችግር መፍቻ ቁልፍ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review