የመዲናዋን ስማርት ኢኮኖሚ ለመገንባት እና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ገለጹ

You are currently viewing የመዲናዋን ስማርት ኢኮኖሚ ለመገንባት እና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ገለጹ

AMN ህዳር 10 /2018 ዓ.ም

‎የአዲስ አበባ ከተማ ስማርት ኢኮኖሚ ለመገንባት እና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሰው ሰራሽ አስተውሎት በእጅጉ ይጠቅማል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር በኢትዮጰያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጰያ በአለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ውድድረ በንቃት መሳተፏን የሚያረጋግጥ መንገድ መድረሱን መግለፃቸው ይታወሳል ።

‎ይሀንን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጰያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችውን እምርታ ጎብኝተዋል ።

‎በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከኤ ኤም ኤን ጋር በበራቸው ቆይታ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰራው ስራ በከተማ ደረጃ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን እና አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ተግባራት በላቀ ደረጃ ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል።

‎እንደ ኢትዮጰያ ላሉ ሃገሮች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በፍጥነት ለማደግ እና ተወዳዳሪ ለመሆን እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል ።

‎አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ደህንነትን ለማረጋገጥ ፣ልማትን ለማፋጠን ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማገዝ በእጅጉ ይጠቅማል ያሉት ምክትል ከንቲባው ፣ በተለይም ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ልውውጥ እንዲኖር ለማስቻል ያግዛል ብለዋል ።

ቴክኖሎጂዉ የኮሙኒኬሽን አገልግሎትና ሃብት አስተዳደር ጨምሮ የትራንስፖርት ፣ የቤቶች ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጉብኝታቸው መገንዘባቸውን አስረድተዋል ።

‎በተለይም በመዲናዋ በሀብረተሰቡ ቅሬታ የሚነሳባቸው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ነው የተናገሩት ።

‎ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፣ ለነዋሪዎች ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት የምትሰጥ ስማርት ከተማ ለማድረግ በርካታ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወጤቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል ።

‎ከተማዋ ልምታልመውን የእድገት ጉዞን ለማፋጠን ዘመኑን የዋጁ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን መረዳታቸውን ጠቁመዋል ።

‎የከተማዋ የዕለት ተዕለት ስራ መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ መስጠት መቻል እንደሚገባ በጉብኘታቸወ ወቅት መገንዘባቸውን የገለፁት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲሰ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ናቸው ።

‎በከተማዋ ላይ የሚሰሩ ግንባታዎችን ለመከታተል ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ወሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መረጃ ማቀናጀት ወሳኔ ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ውጤቶችን በጉብኝታቸው ማየታቸውን ነው የገለጹት ።

‎የከተማ ገጽታን ከመቀየር አንፃር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ጀማሉ ጀንበሩ (ዶ/ር) ናቸው ።

ከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው ፣ በቅርቡ ይፋ የተደረጉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሽ መሆኑን አስረድተዋል ።

‎በቀጣይ ለብልሹ አሰራር የተጋለጡ አሰራሮችን ለመቅረፍ ከኢትዮጰያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review