በዓለም ላይ ከሚታወቁ ሁለት ፐርሰንት ምሁራን መካከል አንዱ የሆነው – ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ

You are currently viewing በዓለም ላይ ከሚታወቁ ሁለት ፐርሰንት ምሁራን መካከል አንዱ የሆነው – ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ

‎AMN ህዳር 10/2018

‎ዶክተር ጂኔኑስ ፍቃዱ ተማራማሪ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቻይና ሆንግ ኮንግ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የድህረ ምረቃ ዶክትሬት (Post Doctoral) ትምህርቱን በመከታተል ትምህርቱን አገባዷል።

‎ይህ ተመራማሪ ላለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት አመርቂ የሚባል ውጤት አስመዝግቧል፡፡

‎ሳንፎርድ ዩኒቨርስቲ ይህንን ተመራማሪ አስመልክቶ ሰሞኑን ያወጣው መረጃ ደግሞ የዓለም መነጋገሪ ሆኗል፡፡

‎ይህም ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ የምርምር ጽሁፋቸዉ በበርካቶች ዘንድ ለማጣቃሻነት ከሚውሉ የአለማችን ሁለት ፐርሰንት ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሊሆን መቻሉ ነው፡፡

‎የወለጋ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበረዉ ዶ/ር ጂኔኑስ በወጣትነት እድሜው በፋርማሲ ሳይንስ ይታወቃል፡፡

‎ ከ100 በላይ የምርምር ጽሁፎችንና መጽሄቶችን በማሳተምም አለም አቀፍ እዉቅና አግኝቷል፡፡

‎በአሁኑ ወቅት በሳንፎርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎችና የተለያዩ ምርምሮችን የሚያካሄዱ ተመራማሪዎች የአለም ሳይንቲስቶች ካሳተሟቸዉ በርካታ የምርምር ጽሁፎች መካከል የዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ የምርምር ጽሁፎች የመጀመሪያዉ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

‎ይህንን ተከትሎም ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ በአለም ላይ ከሚታወቁ ሁለት እጅ ምሁራን አንዱ ሊሆን በቅቷል፡፡

‎ከዚህ በተጨማሪም በሆንግ ኮንግ ዩኒቨርስቲ አመርቂ ስኬት ካስዘገቡ 6 ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሊሆን ችሏል፡፡

‎”ይህ ስኬት ከፈጣሪ የተገኘ ነው፤ ለሶስት አመታት ከነዚህ ተመራማሪዎች አንዱ በመሆኑ ደስታ ይሰማኛል” ሲል ይህ ወጣት ምሁር ሃሳቡን አጋርቷል፡፡

‎በ2023 በ5ሺህ 445 ምርምሮች ላይ የጂኔኑስ የምርምር ጽሁፎች የተጠቀሱ ሲሆን በ2024 በ3ሺህ 148 ምርምሮች ላይ እንዲሁም በ2025 በ1ሺህ 717 ጽሁፎች ላይ ስራዎቹ በዋቢነት ተጠቅሰዋል፡፡

‎ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ በወለጋ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሲሆን እዚያዉ በመምህርነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

‎ኋላ ላይ ግን ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ውጪ ሃገር ተልኮ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡

በመልካሙ አበበ

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addisababa

#addisababa

#education

#hongkong

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review