በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን ደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ የዲቻ ቀበሌ ከአመታቶች በፊት ለመኖርም ሆነ ለማምረት የሚታሰብ አልነበረም፡፡
ነገር ግን ዛሬ ላይ ይህ ቀበሌ የበርካቶች መኖሪያ፣ የሙዝ፣ የፓፓያ እና አቮካዶ ምርቶች መገኛ ሆኗል፡፡
ጦም የሚያድሩ መሬቶችን ወደ ምርትና ስራ አጥ ወጣቶችንም ወደ ስራ የማስገባት የመንግስት እቅድ በየም ዞን ደሪ ሳጃ ቀበሌ በተግባር ተገልጧል፡፡
ለአመታት ስራ ያልነበራቸው ወጣቶች በሰራተኛ እጆቻቸው በርሀን ወደ ልምላሜ ቀይረው አንድም ራሳቸውን በሌላ መልኩ ደግሞ ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ እየደጎሙ ነው፡፡
20ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን ደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ እየለማ ያለውን የሙዝ እና የፓፓያ ክላስተር ተጎብኝቷል፡፡
በተመስገን ይመር