አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አሰባሳቢ ሀገራዊ ትርክትን በመገንባት ረገድ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አሰባሳቢ ሀገራዊ ትርክትን በመገንባት ረገድ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

AMN ኅዳር 11/2018 ዓ.ም

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራርና ሰራተኞች 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የፖናል ውይይት አካሂደዋል፡፡

በፖናል ዉይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ የፌደራሊዝም ስርዓት ብዝኃነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩል ተሰሚነት እንዲኖራቸው ከፍተኛ ሚና ያለው ስለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ጣቢያው የብዝኃነት ድምጽ ምሳሌ መሆኑን የገለጹት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ፤ በአምስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለአድማጭ ተመልካቾች መድረስ መቻሉ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም በሌሎች ቋንቋዎች ማህበረሰቡን የመድረስ ውጥን እንዳለም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የጠቆሙት፡፡

ብዝኃነት ውበት ከመሆኑም ባሻገር ሀይልን የሚፈጥር በመሆኑ በምጣኔ ሀብት፤ በፖለቲካው እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ላይ ለውጥ ማስመዝገብ የሚቻል መሆኑን ገልጸው፤ነጠላ ትርክትን በማስቀረት የወል ትርክት ላይ አበክሮ በመስራት ሀገራዊ ትርክትን ማጽናት እንደሚቻልም ጭምር ነው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ አጽንኦት የሰጡበት፡፡

20ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በተካሄደው የፖናል ውይይት ላይ የተገኙት የተቋሙ ሰራተኞችም ፤ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ከማጉላት አንጻር ሚዲያ አይተኬ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

በይትባረክ ኢሳያስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review