የዓለማችን እህትማማቾቹ ከተሞች አዲስ አበባ እና ኳላ ላምፑር
አዲስ አበባ
በምሥራቅ አፍሪካ ትገኛለች
የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋና ከተማ
ከኒውዮርክ እና ጄኔቭ ቀጥሎ 3ኛዋ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከተማ
በፈጣን የከተሜነት ዕድገት ላይ የምትገኝ
የውብ ባህሎች፣ ማንነቶች እና ቋንቋዎች መገኛ
በመሠረተ ልማት ረገድ ከቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ የምትመደብ
በተለይም የኮሪደር እና ልዩ ልዩ ፓርኮች ግንባታ ከተማዋን ዓለም አቀፍ የኮንፍረንስና የቱሪስት መዳረሻ አድርጓታል
በ2017 ዓ.ም ብቻ ከአንድ ሚሊየን በላይ የውጭ ቱሪስቶች የጎበኟት ከተማ ናት
አዲስ አበባ የኳላ ላምፑር እህት ከተማም ናት
ኳላ ላምፑር
የማሌዥያ ዋና ከተማ
ደቡብ ምሥራቅ ኢስያ ትገኛለች
የሀገሪቱ የአስተዳደር፣ ፋይናንስ፣ ቱሪዝም፣ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ማዕከል
የማላይ፣ ቻይና እና ህንድ ማንነት እና ድንቅ ባህሎች መገኛ
ቱሪዝም በ2024 ብቻ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከ15 በመቶ በላይ ድርሻ ነበረው
16.5 ሚሊየን የውጭ ቱሪስቶችም በ2024 የጎበኟት ከተማ ናት
ኳላ ላምፑር የአዲስ አበባ እህት ከተማም ናት