ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የአሜሪካን የሰላም ዕቅድ እንደሚቀበሉ አስታወቁ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የአሜሪካን የሰላም ዕቅድ እንደሚቀበሉ አስታወቁ

AMN- ህዳር 12/2018 ዓ.ም

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለመቋጨት በአሜሪካ የቀረበውን ረቂቅ የሰላም ዕቅድ ከተቀበሉ በኋላ፣ ከአሜሪካ ጋር በታማኝነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ረቂቅ ዕቅዱ ዩክሬን በቁጥጥሯ ስር ያሉትን በምስራቅ ዩክሬን የሚገኙ የዶንባስ አካባቢዎችን መልቀቅ፣ የወታደሮቿን ቁጥር መቀንስን እና ኔቶን ፈጽሞ ላለመቀላቀል ቃል መግባትን ያካተተ መሆኑን በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ተመላክቷል።

በረቂቅ ዕቅዱ አሜሪካ ሁለቱንም ወገኖች እኩል ማሳተፏን የኋይት ሀውስ ፕሬስ ጸሐፊ ካሮሊን ሌቪት ተናግረዋል።

የዜለንስኪ ጽህፈት ቤት ባወጣው ልዩ መግለጫ፣ “ዩክሬን ጦርነቱ እንዲያበቃ የእቅዱን ድንጋጌዎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመተግበር ተስማምታለች” ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ዕቅዱን አስመልክቶ በሚቀጥሉት ቀናት ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደሚወያዩም ተናግረዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review