በ19ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብስክሌት ብሔራዊ ቡድን ሌላ ወርቅ አሳክቷል።
64 ኪሎ ሜትር በፈጀው የጎዳና ላይ ውድድር ፅጌ ካህሳይ የወርቅ ማዳልያ ለሀገሯ ማስገኘት ችላለች።
ብስክሌተኛዋ ትላንት በግል የሰዓት ሙከራ ወርቅ ማምጣቷ ይታወሳል።
በዛሬው ውድድር ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ቅሳነት ግርማይ 3ኛ ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ራሄል ታመነ 4ኛ ወጥታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ